የኮሮናቫይረስን ለማከም ይረዳል የተባለው የሙከራ መድኃኒት በስፋት ሊመረት መሆኑ ተገለፀ

0
918

የኮሮናቫይረስን ለማከም ይረዳል የተባለውን የሙከራ መድኃኒት በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ አገራት ለማዳረስ በሚያስችል መጠን እንዲመረት ከተለያዩ መድኃኒት አምራች ተቋማት ጋር ስምምነት ተደርሷል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ መዳኒቱ በስፋት እንዲመረት በተለያዩ ሀገራት ከሚገኙ የመድሀኒት አምራቾች ጋር ስምምነት የተፈራረመው ሬምዴሲቬር የተባለውና ለኢቦላ በሽታ ህክምና ሲውል የቆየውን መድኃኒት ባለቤት የሆነው ኩባንያ ነው፡፡

የጸረ ቫይረስ መድኃኒቱን በማምረት በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ 127 አገራት ለሽያጭ እንዲያቀርቡ ፈቃድ ያገኙት በህንድና በፓኪስታን ውስጥ የሚገኙ አምስት የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች ናቸው።

ጊሌድሳይንስስ እንዳለው ከመድኃኒት አምራቾቹ ጋር የተደረሰው ስምምነት መድኃኒቱን የማቅረቡ ተግባር ከሞላ ጎደል ሁሉንም የኣለማችንን ከፍተኛ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን አገራትን እንደሚያካትት ተገልጿል።

ከሳምንት በፊት አሜሪካና ጃፓን ሬምዴሲቬርየተባለውን ይህንን መድኃኒት የኮሮናቫይረስ ህሙማንን ለማከም ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ መስጠታቸውም የሚታወስ ነው ሲል ቢቢሲ አማርኛ በዘገባው አስታውሷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here