ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3410 የላብራቶሪ ምርመራ አርባ ስድስት (46) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡
በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሰባት መቶ አንድ (701) ደርሷል፡፡
በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት የኮሮና ቫይረስ በምርመራ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ አንድ የ32 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ ኢትዮጵያዊት ትናንት ለሊት ህይወቷ በማለፉ በሀገራችን በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 6 መድረሱ ከጤና ሚኒስትር ዘገባ ለማወቅ ተችሏል፡፡





