በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ 73 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

0
708

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገው 2844 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 73 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 49 ወንድ እና 24 ሴት ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ6 እስከ 75 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡

ከእነዚህም 73 ግለሰቦች ውስጥ 67ቱ ሰዎች በዜግነት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ቀሪዎቹ 6 ሰዎች የተለያዩ ስድስት ሀገራት ዜጎች መሆናቸውም ከመግለጫው ለማወቅ ተችሏል፡፡

እንደ ጤና ሚኒስትር ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ መግለጫ ቫይረሱ በምርመራ እንደተገኘባቸው ከተረጋገጠባቸው ሰዎች ውስጥ 56ቱ ከአዲስ አበባ (13ቱ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ 12ቱ የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው እንዲሁም 31 ሰዎች የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ሲሆኑ በተጨማሪም 4 ሰዎች ከትግራይ ክልል (የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው) ፣ 2 ሰዎች ከአማራ ክልል (በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው) ፣ 8 ሰዎች ከሶማሊ ክልል (የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው እንዲሁም 3 ሰዎች የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው የድንበር ተሸጋሪ መኪና አሽከርካሪዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ይህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙትን ሰዎች ቁጥር 655 ያደረሰው መሆኑም ታውቋል፡፡

በተጨማሪም በትናንትናው እለት 7 ሰዎች (4 ሰዎች ከደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል እንዲሁም 1 ሰው ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ በአጠቃላይ በሀገራችን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 159 መድረሱን ከሚኒስትሯ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here