ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኮሮና ቫይረስ ወርርሽኝን መከላከል ላይ ያተኮረ መልዕክት ዛሬ በማህበራዊ ገፃቸው አስፈርዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስተሩ በመልዕክታቸውም የኮሮና ወዳጅ ማን እንደሆነ ደርሰንበታ፣ መዘናጋት ይባላል፡፡ ኮሮና ከመዘናጋት ጋር ከተባበረ አንችለውም ሁለቱን መነጣጠል አለብን ሉ ሲሆን ሰሞኑን በኮሮና የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ የመሄዱ ምክንያት ኮሮናና መዘናጋት ግንባር በመፍጠራቸው መሆኑን አሳስበዋል።
በተጨማሪም ኮሮና ማንን እንደሚጠላና እንደሚፈራ ዐውቀነዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ኮሮና ጥንቃቄ የሚባለውን ፈጽሞ አይወደውም፣ ጥንቃቄ ባለበት ወይ አይደርስም ፤ ወይ የከፋ ጉዳት አያደርስም ብለዋል፡፡
እንደምታዩት ሁለት፣ ሦስት፣ ዐሥር፣ ሠላሳ፣ ሰባ፣ እያለ መቶ ገብቷል።
ሁኔታው የሚያሳየው ኮሮና እያመረረ፣ እኛ እየተዘናጋን መምጣታችንን ነው።
ኮሮና ተዘናግቶ እኛ ብናመር ነበር ጥሩ።
ወይ ተባብረን እንነሣበት፤ አለያም ኮሮናና መዘናጋት ተባብረው ይደቁሱን?
ምርጫው ከሁለቱ አንዱ ነው?
ሁኔታው ሳይመርብን፣ እኛ እናምርበት፣ ኮሮና ሳያሸንፈን እናሸንፈው። ኮሮናን የማሸነፊያ ቀን ዛሬ፣ የማሸነፊያ ሰዓት አሁን፣ የሚያሸንፈውም ሰው እርስዎ ነዎት ብለዋል፡፡



