በ24 ሰአት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 137 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

0
941

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ 5015 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 137 ሰው ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙትን ሰዎች ቁጥር 986 አድርሶታል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 86 ወንድ እና 51 ሴት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ከ4 እስከ 75 አመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውም ታውቋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ 109 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 1 ሰው ከ አፋር ክልል፣ 2 ሰዎች ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ 17 ሰዎች ከአማራ ክልል እንዲሁም 8 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል የሚገኙ መሆናቸውም ከመግለጫው ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 20 የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 8 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እንዲሁም 109 የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያልነበራቸው መሆኑም ታውቋል፡፡

በተጨማሪም በትናንትናው እለት ከአዲስ አበባ 6 ሰዎች ከበሽታው በማገገማቸው በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 197 መድረሱን ከጤና ሚኒስትር መግለጫ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሌላ በኩል 1 የ62 ዕድሜ ያላቸው ወንድ ህይወት በቫይረሱ ሳቢያ በማለፉ ይህን ተከትሎ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 8 ደርሷል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here