ምክር ቤቱ ምርጫ ለማራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ

0
855

የፌደሬሽን ምክር ቤት ስድስተኛውን ብሄራዊ ምርጫ ለማራዘም የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ውይይት አድርጎ የውሳኔ ሀሳቡን በ114 ድጋፍ፣ በ4 ተቃውሞ እንዲሁም በ1 ድምጸ ተዓቅቦ አፅድቆታል።

ስድስተኛውን ብሄራዊ ምርጫ ለማራዘም የፌደሬሽን ምክር ቤት የህገ መንግስት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውሳኔ ሀሳብ አቅርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ስጋት ሆኖ እስከቀጠለበት ጊዜ ድረስ የሁሉም ምክር ቤቶች ስልጣን እንዲቀጥል ወስኗል።

በተጨማሪም ወረርሺኙ ስጋት አለመሆኑ በአለም አቀፍ የጤና ተቋም ሲረጋገጥ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ይሄንን ካፀደቀ በኀላ ከ9 ወር እስከ 1 አመት ባለ ጊዜ ውስጥ ምርጫ ይካሄድ በሚል የውሳኔ ሀሳብ ላይ ውሳኔ ማስተላለፋን ከኢ.ዜ.አ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here