ኢትዮጵያ በሌሎች ላይ ጉዳት የማድረስ ታሪክ የላትም ፣ አሁን ቢሆን ሌሎችን የመጉዳት ፍላጎት የለንም- ጠ / ሚኒስትር አብይ አህመድ

0
871

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የታላቁን የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በሚመለከት በጠቅላይ ሚኒስተር ፅህፈት ቤት ማህበራዊ ድረ-ገፅ ላይ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

“ ኢትዮጵያ በሌሎች ላይ ጉዳት የማድረስ ታሪክ የላትም ፣ አሁን ቢሆን ሌሎችን የመጉዳት ፍላጎት የለንም፡፡ የእኛ ፍላጎታት አንድ ብቻ ነው – ማደግ እና ብልጽግና። እንዲሁም ህዝባችንን ከድህነት አረንቋ ማላቀቅ ነው።

ከ 50 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን የንፁህ ውሃ አቅርቦት የላቸውም፤ ያ ማለት የአንድ ሀገር ህዝብ ማለት ነው ፡፡ ከ 50 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት የኤሌክትሪክ ኃይል የላቸውም፡፡ እስከ አሁን ድረስ የኢትዮጵያ እናቶች ለማገዶ ፍጆታ የሚውል እንጨትን ይሸከማሉ፡፡ መሰረታዊ መብቶቻቸውን እና ፍላጎቶቻቸውን ማሟላት እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም የታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ለእኛ ለኢትዮጵያውያ እድገት ብሎም ለታችኛው የተፋሰሱ አገራት እኩል አስተዋፅዎ አለው፡፡ ስለዚህ ይህንን ፕሮጀክት በቀና መንፈስ ማየቱ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡”- ጠ / ሚኒስትር አብይ አህመድ

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here