የባህልና ዘመናዊ ሕክምናዎችን አቀናጅቶ መሥራት ላይ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አሳሰቡ

0
767

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ከወሎ ዩኒቨርስቲ፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንዲሁም የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር “በኮቪድ-19 እና በሌሎች ወረርሽኞች ዙሪያ አገር-በቀል የባህላዊ ህክምና እውቀቶች ሊያመጡ የሚችሉት መፍትሄዎች” በሚል ርዕስ ሳምንታዊ የምሁራን ምክክር ዌቢናር በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በዌቢናር ምክክሩም ዶክተር ሊያ ታደሰ ‘‘በዓለም ላይ የተገኙ ግኝቶች ከተፈጥሮ መሠረት ያደረጉ ናቸው’’ በማለት የባህል ሕክምናውን ከዘመናዊው ሕክምና ጋር ማቀናጀት ካልተቻለ ወደፊት መሄድ እንደሚያስችገር አሳስበዋል፡፡

ይህ የምክክር መድረክ ‘‘አገር በቀል ዕውቀቶችን እንዴት አድርገን ወደ ሳይንሳዊ መንገድ እናምጣ? የሚለውን ጉዳይ አትኩሮት እንድንሰጥበት ይረዳናል ያሉት ሚኒስትሯ የባህልና ዘመናዊ ሕክምናዎችን አቀናጅቶ መሥራት በኢትዮጵያ እንብዛም ያልተሞከረ በመሆኑ ይህንን የኮሮና ወረርሽኝ ጊዜ እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ከባህል ሐኪሞች ጋር በመሆን ለአገርም ሆነ ለዓለም የሚጠቅም ሥራ መስራት የሚቻልበት ተስፋ እንዳለም ጠቁመዋል፡፡

በምክክሩ ላይም የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሒሩት ወልደማርያም (ፕሮፌሰር)፣ የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶክተር)፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሒሩት ካሳው (ዶክተር) እና ሌሎችም የዘርፉ ምሁራን እየተሳተፉበት እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here