የከፍተኛ ትምህርት ዘርፉን ለማጠናከር የሚውል የ1 ሚሊዮን ዶላር የፕሮጀክት ድጋፍ ተገኘ

0
1051

የከፍተኛ ትምህርት ዘርፉን በዓለም አቀፋዊነት እና በአመራርና አስተዳደር መስክ ለመደገፍ ያለመ የ1 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ድጋፍ መገኘቱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ኢትዮጵያ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ቢሮ የዩኒቨርሲቲ አጋርነት በኩል በሚመራው የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል የ1 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ድጋፍ ለማግኘት መመረጧን በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኢምባሲ ለሚኒስቴሩ በላከው መልዕክት ገልጿል፡፡
ከዚህ ቀደም በአሜሪካ ፉል ብራይት ፕሮግራም፣ የአምባሳደርስ ዲስቲንጉሽድ ስኮላርስ ፕሮግራምና ያሊ የተሰኙ ፕሮግራሞች ነፃ ትምህርቶችን በመስጠት ድጋፍ እንደሚደርግ ጠቅሰው አሁን ደግሞ እውቀትን ማካፈልና መልካም ተሞክሮዎችን ማስፋፋት ዓላማው ያደረገ ድጋፍ ማድረጉን ኤምባሳው ገልጿል፡፡
ድጋፉ በአሜሪካና ኢትዮጵያ መካከል ከ70 ዓመታት በላይ የዘለቀ ትብብርን ለማጠናከር ያግዛል ተብሏል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመወያየት ባለፈው ዓመት ወደ አሜሪካ ማቅናታቸው እና ያንንም ተከትሎ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ጸሃፊ አምባሳደር ቲቦር ናዥ በያዝነው ዓመት ጥር ወር ላይ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 84 ሠኔ 6 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here