የተባበሩት መንግስታት ደርጅት ሜጀር ጄነራል ከፍያለው አምዴ ተሰማን በአብዬ ለሚገኘውን የመንግስታቱ የፀጥታ ኃይል ሃላፊ አድርጎ ሾመ

0
1120

የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ  ሜጀር ጄነራል ከፍያለው አምዴ ተሰማን በአብዬ ለሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው  ኃይል ዋና ሃላፊ አድርጎ  መሾሙን አስታውቀዋል፡፡

ሜጀር ጄነራል ከፍያለው በሐምሌ ወር ስራቸውን በሚያጠናቅቁት ሜጀር ጄኔራል መሃሪ ዘውዴ ገብረማሪያም ቦታ መሾማቸውን የገለፁት ዋና ፀሃፊው ሜጀር ጄነራል መሃሪ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እስካሁን ላከናወኑት ውጤታማ አመራራዊ ሚና የመንግስታቱ ድርጅት ምስጋናው ላቅ ያለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሜጀር ጄነራል ከፍያለው አምዴ ተሰማ ከ30 ዓመት በላይ የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ውስጥ ልዩ የወታደራዊ ሙያ ልምድ ያላቸው ሲሆን  ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የምክር ቤት አባል ሆነው አገልግለዋል፡፡ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሰራዊት የምህንድስና ክፍል ዋና ሃላፊ ሆነው አገልግለዋል ፡፡ በዚህም በእቅድ በማውጣት፣ በማስተባበር፣ በመምራት፣ የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሆም ተዛማጅ በሆኑ የምህንድስና እንቅስቃሴዎች ላይ ጉልህ ሚናን ሲጫወቱ ቆይተዋል።

ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር ከ2012 እ.ኤ.አ  እስከ 2016 እ.ኤ.አ  በኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች የመምሪያው አዛዥ፣ በ2015 በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ሴክተር ኮማንደር፣ ከ2016 እ.ኤ.አ. እስከ 2017 እ.ኤ.አ ምክትል ማዕከላዊ እዝ አዛዥ እንዲሁም ከ2017 እ.ኤ.አ  እስከ 2018 እ.ኤ.አ የምእራብ ጦር እዝ አዛዥ ሆነው አገልግለዋል፡፡

እንደ እ.ኤ.አ 1963  በአርሲ የተወለዱት ሜጀር ጄኔራል ከፍያለው ከዩናይትድ ስቴትስ አሽላንድ ዩኒቨርስቲ በቢዝነስ አስተዳደር ማስተርስ፣ እንዲሁም ከሩሲያ ፌዴሬሽን የውትድርና ኃይል አካዳሚ  ወታደራዊ አንድነት ምስረታ እና መቆጣጠር የመጀመሪያ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን እንግሊዘኛ እና የሩሲያ ቋንቋን በብቃት እንደሚናገሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here