ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበርበር ተያዘ

0
725

ከሰኔ 6-10 2012 ባሉት ቀናት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮንትሮባንድ አቃዎች እና የንግድ ማጭበርበር ተግባራት መያዙ ተነለፀ፡፡
ከ16 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ንግድ ማጭበርበር ተግባራት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በሁሉም የአገሪቱ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎችና ኬላዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ክትትል ተደርጎ ንብረቶቹ የተያዙ ሲሆን የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም የኮንትሮባንድና የንግድ ማጭበርበር እንቅስቃሴዎችን የመቆጣጠር እና የማጋለጥ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል የተለያዩ ዓይነት አዳዲስና አሮጌ አልባሳት፣ የአዋቂና የህፃናት ጫማዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ ጎማና መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይት፣ ጫት፣ ሃሺሽ እና ልዩ ልዩ ዓይነት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ይገኙበታል፡፡
እንዲሁም በቦሌ፣ በሞጆ እና በአንዳንድ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ በተደረገው ቁጥጥር ብዛት ያላቸው የንግድ ማጭበርበር እንቅስቃሴዎች ተለይተው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረገ ሲሆን 120,000 ሀሰተኛ ዶላርም በሞያሌ ቅርንጫፍ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 85 ሠኔ 13 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here