የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለሲዳማ የክልልነት ሥልጣን አስረከበ

0
468

በ5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤው በሰኔ 11 ቀን 2012 ከሰዓት በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በአዳዲስ መዋቅሮች ለመደራጀት በቀረበ ጥያቄ፣ ምላሽ እና የውሳኔ ሀሳብ ላይ የመከረው የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለአዲሱ የሲዳማ ክልል ሥልጣን አስረክቧል፡፡
በመሆኑም አዲሱ የሲዳማ እና ነባሩ የደቡብ ክልሎች ዛሬ በይፋ ተፋትተዋል፡፡
የሲዳማን ዞን በክልል ደረጃ ለማደራጀት ኅዳር 10 ቀን 2012 በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ዞኑ የኢትዮጵያ 10ኛው ክልል ለመሆን በሕዝበ ውሳኔው ለመሳተፍ ከተመዘገበው ሕዝብ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆነውን፣ ማለትም 98.51 በመቶ ድምጽ ማግኘቱን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በወቅቱ መግለጹ ይታወቃል፡፡
በክልሉ ሌሎች አካባቢዎችም እየተነሱ ያሉ የመዋቅር ጥያቄዎች በተገቢ መልኩ እንዲታዩ መንግሥትና የሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲሰጥ ምክር ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል ።
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ የ2012 በጀት ዓመት ከ2 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ረቂቅ በጀት ላይ በመምከር አጽድቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 85 ሠኔ 13 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here