ከ38 ሺ በላይ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ተደረገ

0
868

ከ 38 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ( ኢንትርፕርነሮች) የማምረቻ መሳሪያዎች እንዲሁም ሌሎች አጋዥ እቃዎችን እንዲያገኙና የኤሌክትሮኒክስ ግበይት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርግ ስምምነት ተደረገ፡፡ ስምምነቱ በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ የሚደረጉ የልማት ትብብሮችን ማህበረሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ለሃገር ሁለንተናዊ ልማት የሚኖሯቸው ፋይዳ አመላካች መሆኑም ተመላከተ፡፡
በሴቶች እንተርፕርነርሺፕ ልማት ፕሮጀክት በሶስት የብድር እና ፋይናንስ አቅራቢ ድርጅቶች እና ከአንድ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ተቋም ጋር ተደረገውን ስምምነት አስመልክቶ የፌደራል ከተሞች የስራ እድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዋና ዳይሬክተር ገብረ መስቀል ጫላ በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት ስምምነቱ በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ እየተደረጉ ለሚገኙ የልማት የትብብር ስራዎች እንደ አብነት ከሚቆጠሩ ተግባራት መካከል ይጠቀሳል፡፡
በፌደራል ከተሞች የስራ እድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ስር የሚገኘው የሚገኘው የሴቶች ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ፕሮጀክት በተለያየ መስክ ተሰማርተው መስራት ስለሚፈልጉ ውጤታማ ሴት ኢንተርፕርነሮች ለስራ መስኬጃ የሚሆን መነሻ ካፒታል በብድር መልክ በማመቻቸት ተጨማሪ ስልጠና በመስጠት በዘርፉ የሚደረገውን እስቅስቃሴ በበላይነት ሲያስተባብር መቆየቱንም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ከሶስት የብድርና ፋይናንስ አቅራቢ ድርጅቶች ከአንድ የክፍያ አገልግሎት ተቋም ጋር መተባበር ሴት ኢንተርፕርነሮች ማምረቻ መሳሪያዎችንና ዕቃዎችን በብድር የሚያገኙበት መንገድ ማመቻቸቱን አስመልክተዋል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 88 ሐምሌ 4 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here