10ቱ በ2012 በጀት ዓመት ከፍተኛ የመደበኛ ወጪ በጀት የተመደበላቸው ዩኒቨርሲቲዎች

Views: 887

ምንጭ: ምንጭ: የ2012 የፌደራል መንግሥት በጀት(በነጋሪት ጋዜጣ የታተመ)

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመጪው የበጀት ከፍተኛ የመደበኛ እንዲሁም የካፒታል በጀት ከተያዘላቸው ዘርፎች ትምህርት ቀዳሚው ሲሆን በተለይም ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተያዘው በጀት ከፍተኛ ድርሻ ይይዛል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የተባለው መደበኛ ወጪ የተመደበለት ሲሆን ሌሎች ሰባት ዩኒቨርሲቲዎች በተመሳሳይ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦላቸዋል።

ከዩኒቨርሲቲዎቹም አዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ ከፍተኛ ገቢ በማስገባት ከተመደበለት በጀት 81.9 ሚሊዮን ብሩን ካመነጨው ገቢ መሸፈን የቻለ ሲሆን መቀሌ ዩኒቨርሲቲ 60.4 ሚሊዮን ብር ማመንጨት ችሏል።

ለዩኒቨርሲቲዎቹ ለመደበኛ ወጪ ከተመደበላቸው ገንዘብ ባሻገር ለካፒታል ወጪዎችም ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦላቸዋል። የፌደራል ዋና ኦዲተር በተደጋጋሚ በሚያርበው ሪፖርት መሰረት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የአገሪቱን ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ተቀባይ ቢሆኑም በበጀት አፈፃፀም እና ሪፖርት ላይ ከፍተኛ ጉድለት የሚታይባቸው ናቸው።

ቅጽ 1 ቁጥር 36 ሐምሌ 6 2011

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com