በድምፀ ወያኔ፣ በኦኤምኤን እና በአስራት ሚዲያ የወንጀል ምርመራ ተጀመረባቸው

0
416

በድምፀ ወያኔ ቴሌቪዝን፣ በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ(ኦኤምኤን) እና በአስራት ሚዲያ ላይ በተለያዩ ጊዜያት ብሔርን ከብሔር በማጋጨት ተጠርጥረው የወንጀል ምርመራ እንደተጀመረባቸው የጠቅላይ አቃቡ ህግ አስታወቀ፡፡ የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ የተደራጁና ድንበር ተሻ ጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት አቶ ፈቃዱ ፀጋ ለመገናኛ ብዙኃን እንዳስታወቁት፣ በአዲስ አበባ ስቲዲዮ ባላቸው በድምፀ ወያኔ ቴሌቪዝን፣ በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ(ኦኤምኤን) እና በአስራት ሚዲያ ላይ የምርመራ ፈቃድ ከፍርድ ቤት በመውሰድ ምርመራ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
በገናኛ ብዙኃኖቹ ላይ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ምርምራ የጀመረው፣ በተለያዩ ጊዜያት አንዱን ብሔር ከሌላው ብሔር ጋር ሊያጋጩ የሚችሉ መረጃዎችን ማስራጨታቸውን የሚጠቁሙ መረጃዎች በመገኘታቸው መሆኑን ፈቃዱ አስታውቀዋል፡፡ ፈቃዱ አክለውም የምርመራ ሂደቱ የሚከናወነው ቀደም ሲል በመገናኛ ብዙኃኖቹ ከተላለፉ መረጃዎች ጀምሮ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በአርቲስት ሀጫሉ ሁንደሳ ግድያ ሰበብ በአዲ አበባ እና በተለያዩ በኦሮሚያ ክልል ከተሞች በተፈጠረው ኹከት ተገቢ ያልሆነ መረጃ በማሰራጨት እንዲሁም ህዝብን ወደ ብጥብጥ የሚከት ቅሰቀሳ በማድረጋቸው የትግራይ ቴሌቪዥን እና ድምፀ ወያኔ ቴሌቪዥን የሳታላይት ስርጭታቸው እንድቋረጥ ተደርጓል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 88 ሐምሌ 4 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here