የትምህርት ጥራቱን በዘላቂነት ለመፍታትም በ 2014 ወደ ተግባር የሚገባ አዲስ ስርዓተ ትምህርት እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።
እንዲሁም በትምህርት ሚኒስቴር የተላላፈው ከ 8ኛና 12ኛ ክፍል ውጪ ያሉ ተማሪዋች ነፃ ዝውውር ተማሪዋች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማበረታታት መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታወቋል ።
የተማሪዎች ነፃ ዝውውር ውሳኔ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ ያለመ መሆኑንም የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በነፃ የተዘዋወሩ ተማሪዋች የትምህርት ምዕራፉ ሲጀመር በተዘዋወሩበት የትምህርት ክፍል ባለፈው የትምህርት ምዕራፍ ላይ ማካካሻ ወስደው ቀጣዪን የትምህርት መርሃ ግብር የሚቀጥሉ ይሆናል ብለዋል።
ውሳኔው በኮሮና ምክኒያት ተቋርጦ የነበረው የትምህርት መርሃ ግብር ሲጀመር ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማበረታታት እና ወረርሽኙ የፈጠረውን ጫና ለመቀነስ የታሰበ ነው ሰሉ ሚኒስትሩ የገለጹ ሲሆን በአሁን ሰዓት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ያለነው ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት መመለስ ላይ ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይም ተማሪዋች ወደ ትምህርት ቤት ከተመለሱ በኋላ የትምህርት ጥራቱ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በኮሮና ወረርሽኝ ምክኒያት ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ከ 26 ሚሊየን በላይ ተማሪዋች ከ ትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ቅጽ 2 ቁጥር 93 ነሐሴ 9 2012



