የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን የቴክኒክ ኮሚቴ ሰየመ

0
634

የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን የጥናት እና ምርምር ሥራዎችን የሚከታተል እና ድጋፍ የሚያደርግ 7 አባላት ያሉት የትንተና እና ምርምር የቴክኒክ ኮሚቴም ማቋቋሙን አስታወቀ። ኮሚሽኑ የ2012 በጀት ዓመት ሪፖርት እና የ2013 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት ጸድቋል።
በውይይቱ በ2012 በጀት ዓመት የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የነበሩ ደካማ ጎኖች ደግሞ በ2013 በጀት ዓመት እንዲታረሙ የኮሚሽኑ አባላት አሳስበዋል።
በተለይም ከክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ጋር የተደረገው የትውውቅ እና የውይይት ፕሮግራም እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች በሚነሱ የአስተዳደር ወሰን እና ማንነት ጉዳዮች ዙርያ ጥናት እና ምርምር ለማካሄድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተደረሰው ስምምነት የኮሚሽኑ ጠንካራ ጎን ሆኖ ተጠቅሷል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረው ጥናት እና ምርምር በተያዘለት ጊዜ ተጠናቅቆ የታለመለትን ግብ እንዲመታ አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ የኮሚሽኑ አባላት ጠይቀዋል።
አባላቱ እቅድ እና ሪፖርቱን ከመገምገም ባለፈም በአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ዙርያ በኮሚሽኑ የሚሠሩ የጥናት እና ምርምር ሥራዎችን ለመከታተል እና ድጋፍ ለማድረግ እንዲያመች የተዘጋጀውን የትንተና መመርያ መርምረው አጽድቀዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 93 ነሐሴ 9 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here