የባህርና የሎጂስቲክስ አገልግሎት ከ25 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ

0
624

የኢትዮጵያ ድርጅት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ25 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ:: ድርጅቱ በተያዘው በጀት ዓመት የተጀመሩትን ፕሮጀክቶች በማጠናቀቅ የአዳዲስ ፕሮጀክቶች ግንባታ ለመጀመር ማቀዱንም አስታውቋል። የኢትዮጵያ የባህርና የሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በ2011 በጀት ዓመት አጠቃላይ ገቢው 18 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የነበር ሲሆን ባለፈው በጀት አመት የ37 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሮባ መገርሳ እንደተናገሩት ለገቢው ስኬት በተለይ የስንዴና ማዳበሪያ ማጓጓዝ የጎላ ድርሻ ነበረው። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ድርጀቱ አጠቃላይ 11 ሚሊዮን ቶን ገቢና ወጭ የጭነት አገልግሎት መስጠቱንም ተናግረዋል። በተያዘው የ2013 በጀት ዓመት ድርጅቱ 12 ነጥብ 3 ሚሊዮን ቶን በማጓጓዝ 37 ቢሊየን ብር ለማግኘት አቅዶ እየሰራ መሆኑን ተጠቁሟል፡፡ ድርጅቱ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ከማጠናቀቅ በተጨማሪ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር መዘጋጀቱን አመላክቷል።

ቅጽ 2 ቁጥር 93 ነሐሴ 9 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here