ኢትዮጵያ በ2021 እንደሚደርሱ የሚጠበቁ የኮሮና ክትባቶችን በርካሽ ከሚያገኙ 92 ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው አገራት መካከል አንዷ እንደሆነች ዓለም አቀፉ የክትባቶች ትብብር (ጋቪ) መረጃዎች አመልክተዋል።
ጋቪ ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ደረጃቸውን የጠበቁ አንድ መቶ ሚሊዬን የቫይረሱን ክትባቶች በፍጥነት ለማምረት የሚያስለውን ሰምምነት ሴረም ከተሰኘው የህንድ የክትባቶች አምራች ተቋም ጋር ስምምነት ፈጽሟል፡፡
ሴረም አስትራ ዜናካ እና ኖቫቫክስ በተባሉ የምርምር ተቋማት በመዘጋጀት ላይ ያሉ ክትባቶችን ነው የሚያመርተው።
የጋቪ ቦርድ እውቅና የሰጣቸው 92ቱ ሃገራትም ኮቫክስ በተሰኘው የትብብሩ አዲስ የፋይናንስ ስርዓት በመታገዝ ክትባቶቹን ከሶስት ዶላር (መቶ አስር ብር ገደማ) ባልበለጠ ዋጋ የሚያገኙ ይሆናል ተብሏል።
የስርዓቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተመረጡ 92 አገራት ዝርዝርም ባሳለፍነው ሳምንት በጋቢ ቦርድ ጸድቋል።ከነዚህ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ነች፡፡
ቅጽ 2 ቁጥር 94 ነሐሴ 16 2012



