በናዳው ምክንያት ከቆጎታ ወረዳ ኦቴ ቀበሌ 3ሰው ሲሞት አንድ ሰው ላይ ደግሞ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሷል።
በዘኑ የሚገኙ 21 አባወራ 176 የቤተሰብ አባላትም መፈናቀላቸውን የጋሞ ዞን አደጋ ስጋት ስራ-አመራር ጽኀፈት ቤት ኃላፊ ተስፋዬ ማርቆስ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በዞኑ ቁጫ ወረዳ ሾጮራ ቀበሌ በ 2 ቤት ላይ የመስመጥ አደጋ በመድረሱ 5 አባወራ 25 ቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል።
የዝናቡ ሁኔታ ተጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ በተራራማ አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተስፋዬ መርቆስ ማሳባቸውን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።



