በእነ እስክንድር ነጋ ላይ አቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ እንዲያሻሽል ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጠ

0
1522

ፍርድ ቤቱ  እስክንድር ነጋን ጨምሮ በ7 ግለሰቦች ላይ አቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ እንዲያሻሽል ትእዛዝ ሰጥቷል።

 

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የሕገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት አቃቤ ህግ ከዚህ በፊት የመሰረተው ክስ አጠቃላይ ዋስትና ላይ ዝርዝር ክሱን ተመልክቶ ውሳኔ ለማሳረፍ ክሱ ሊሻሻል ይገባል ሲል አዟል።

 

በዚህም አቃቤ ህግ የሚያሻሽለው በሰኔ 23 እና ሰኔ 24 2012 በሰው ላይም በንብረት ላይም ደረሰ የተባለው ጉዳት ተለይቶ እንዲቀርብ፣ የደረሰው ጉዳት ቦታው የት እንደሆነ፣ በየት ክፍለ ከተማ እና ወረዳ፣ በስንት ሰዓት የሚለው መገለፅ አለበት ያለው ፍርድ ቤቱ፤ ቦታው ከታወቀ በኋላም የተከሳሾቹ የወንጀል ተሳትፎ በዝርዝር ተለይቶ እንዲቀርብ አዟል።

 

በዚህ መሰረት አቃቤ ህግ በሳምንት ውስጥ ክሱን አሻሽሎ እንዲቀርብ ለመስከረም 19/ 2013  ጠዋት በችሎት እንዲያቀርብ ማዘዙን ፋና ዘግቧል።

በችሎቱ የተገኙት የእነ እስክንድር አራት ጠበቆች ማረሚያ ቤት ከቤተሰብ ጋር እያገናኛቸው እንዳልሆነ፣ ምግብና ልብስም እየገባላቸው አይደለም ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል።

ሌሎች አቤቱታዎችንም እናቅርብ ያሉት ጠበቆቹ፤ ፍርድ ቤቱ ጥያቄያችሁ በችሎት ተመዝግቦ የሚሄድ አይደለም፤ ክርክር አንዳይነሳበት ሲል ጊዜ የማይሰጡ የህክምና እና በቤተሰብ መጎብኘት ያለባቸውን ማረሚያ ቤቱ እንዲፈፅም ትእዛዝ ሰጥቷል።

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here