ሰሞኑን በጋሞ ዞን እየጣለ ያለው ዝናብ ባስከተለው ናዳ በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

0
1295

በናዳው ምክንያት ከቆጎታ ወረዳ ኦቴ ቀበሌ 3ሰው ሲሞት አንድ ሰው ላይ ደግሞ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሷል።

በዘኑ የሚገኙ 21 አባወራ 176 የቤተሰብ አባላትም መፈናቀላቸውን የጋሞ ዞን አደጋ ስጋት ስራ-አመራር ጽኀፈት ቤት ኃላፊ ተስፋዬ ማርቆስ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በዞኑ ቁጫ ወረዳ ሾጮራ ቀበሌ በ 2 ቤት ላይ የመስመጥ አደጋ በመድረሱ 5 አባወራ 25 ቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል።

የዝናቡ ሁኔታ ተጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ በተራራማ አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ  ተስፋዬ መርቆስ ማሳባቸውን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here