የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በሶስት ዙር ሊቀበል ነው

0
587

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ መከላከልን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ተማሪዎችን በሶስት ዙር ለመቀበል አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጣሰው ወልደሃና (ፕሮፌሰር) እንደገለጹት በኮቪድ 19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊቀንስ ይችላል በሚል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመጀመር ከግንቦት ወር 2012 ጀምሮ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን በኹለት ዙር እንዲገቡ ለማድረግ ዕቅድ ይዞ ዝግጅት ቢያደርግም በኮቪድ 19 የሚያዘው ቁጥር በመጨመሩ ተማሪዎችን በሶስት ዙር ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።

ፕሬዚዳንቱ፤ በአንድ ክፍል ከ25 በላይ ተማሪዎች እንደማይማሩና መምህሩ ደግሞ ከ35 ደቂቃ በላይ ማስተማር እንደሌለበት ተወስኗል ብለዋል

ፕሬዝዳንቱ አክለው ተማሪዎች ፣የአፍ መሸፈኛ ጭንብል (ማክስ) አድርገው፤ መስኮቶች ተከፍተው እንዲማሩ ይደረጋል ማለታቸውን  የዘገበው ኢፕድ ነው።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here