ልደቱ አያሌው በድንገት ከቢሾፍቱ ፖሊስ ጣቢያ ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰዳቸው ተሰማ

0
725

ፖሊስ ልደቱን ለምን  ወደ ፍርድ ቤት እንደወሰዳቸው እስካሁን ምንም መረጃ እንዳሌለው ፖርቲያቸው አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዝደንት  አዳነ ታደስ ‹‹የዋስትና መብታቸውን ፖሊስ እንዲያከብር ለመነጋገር ፍርድ ቤት ቀጠሮ ሰጥቶን እየጠበቅን ባለንበት ሁኔታ ነው ዛሬ ከፖሊስ ጣቢያ ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰዳቸውን የሰማነው›› ሲሉ ለኢትዮ ኤፍኤም የተናገሩት።

አዳነ እንዳሉት ልደቱ ምንም አይነት መጥሪያ እንዳልደረሳቸው ብናውቅም በአንድ ሚዲያ ግን  ልደቱ በሌላ ጉዳይ ክስ እንደተመሰረተባቸው የሚያሳይ ዘገባ ወጥቶ መመልከታቸው በእጅጉ በፍትህ ስርአቱ ላይ ተስፋ እንድንቆርጥ አድርጎናል ነው ያሉት፡፡

ፖሊስ  ልደቱን ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወሰዳቸው በኃላ ስለተፈጠረው ነገር ለማጣራት ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ እየተጓዙ መሆኑንም አዳነ ተናግረዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here