የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ግድያዎችን አወገዘ

0
966

ኦነግ በተለይ ከለውጡ ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ ድንገተኛ ጥቃቶች ግድያዎች እና ከባድ ዝርፊያዎች መበራከታቸውን አስታውቋል።
ይህ በምንም መስፈርት ተቀባይነት የለውም ያለው ኦነግ፤መንግስት በቅድሚያ የዜጎችን የመኖር መብት እንዲከበር የማድረግ ግዴታ አለበት ብሏል።
የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ቀጀላ መርዳሳ እንዳሉት ማንኛውም ዜጋ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን ሲገደል ጥቃቱ የሁላችንም እንደሆነ ሊሰማን ይገባል ብለዋል፡፡
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየደረሱ ያሉት ጥቃቶች መፈናቀሎችና ግድያዎችን ማውገዝ ለአንድ ወገን ብቻ የሚሰጥ ሳይሆን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር የሚንቀሳቀስ የትኛውም የፖለቲካ ፖርቲ ግዴታው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በማይታወቁ ሰዎች እና በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ስለሚገደሉት ዜጎቻችን ሁሌም ቢሆን እንሟገታለን የሚሉት አቶ ቀጀላ የዚህ ግድያ ሰለባዎች የመንግስት አመራሮች ጭምር በመሆናቸው ችግሩ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ መንግስት ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
መንግስት ጸጥታን በማስከበር ህብረተሰቡን ከስጋት ነጻ የሆነ ህይወት እንዲኖረው የማድረጎ ስራ ለዛሬና ለነገ የሚሰጠው ስራ እንዳሆነም ነው የሚናገሩት፡፡
ዘገባው የኢትዮ ኤፍ ኤም ነው

ቅጽ 2 ቁጥር 104 ጥቅምት 21 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here