በአማራ ክልል ሕዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ በነገው እለት ይካሄዳል

0
863

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽኀፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ሰልፉን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም ‹‹መላው የክልላችን ህዝብ፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች ህገ ወጡ የትህነግ ቡድን ያደረሰውን ግፍ እና የአገር ክህደት ወንጀል ለመላው ዓለም በምንችለው ሁሉ ለማሳወቅ የሰልፉ ተሳታፊ አንድንሆን ጥሪ እናቀርባለን›› ብለዋል፡፡

 

ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለጹት ከሆነም ‹‹ ሰልፉ የሚካሄደውም በክልላችን ባህር ዳር፣ ፍኖተ ሰላም፣ እንጅባራ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ ደብረ ታቦር ከተሞች ብቻ ነው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

 

‹‹ከእነዚህ ከተሞች ውጭ ባሉ የክልሉ ከተሞች ሰልፉ የማይካሄደው ህገ ወጡን የትህነግ ቡድን በህግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል በሚደረገው ውጊያ ልዩ የጸጥታ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ነው›› ሲሉም አክለዋል፡፡

 

ሰልፉ ነገ ኀዳር 03/2013 ጠዋት 2፡30 ተጀምሮ በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ሲሆን በተዋቀረው የሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ እና በጸጥታ ኃይላችን ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለት መሆኑንም ከአማራ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here