የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታህሳስ 6 /2013 እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የስታወቀ ሲሆን ከያዝነው ወር ህዳር 22 ጀምሮ ደግሞ በአሮጌው የብር ኖት ግብይት መፈጸም የማይቻል መሆኑም ተጠቁሟል።
ከመስከረም 6/2013 አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።የብር ኖት ቅያሬው በሶስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መወሰኑም ይታወሳል።
ከዚህ ቀን በኋላ በባንኮች አሮጌ የብር ኖት እንደማይኖርም ገልጿል።በዚሁ መሰረት የተፈቀደው የብር መቀየሪያ የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ 25 ቀናት ብቻ እንደቀሩት ይፋ መደረጉን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።



