‹‹የልደቱ አያሌው የጤንነታቸው ሁኔታ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል›› አዳነ ታደሰ

0
1056
ልደቱ አያሌው ዛሬ ኅዳር 11/2013 በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ችሎት ቀርበዋል።
ፍርድ ቤቱም ዐቃቤ ሕግ ክሱን እንዲያሻሽል በማዘዝ፤ ክሱ ግልፅ ባልሆነበት እውነታ የዋስትና መብት ላይ ብይን አልሰጥም ማለቱን የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዝዳንት አዳነ ታደሰ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ አዳነ ታደሰ፤ ችሎቱ በዐቃቤ ሕግ የተጠቀሱት ኸለት አንቀፆች ግልፅነት የሚጎላቸው በመሆኑ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ ውሳኔ ማሳለፉን ገልፀዋል።
ይሻሻል የተባለው ክስ ‹‹ሕገ መንግሥቱን ለማፍረስ በማሰብ የሽግግር ሰነድ ማዘጋጀት›› በሚል የተመሰረተባቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
የተከሳሹን የዋስትና ጥያቄ በተመለከተ ክሱ ግልፅ ባልሆነበት እና ባልተሻሻለበት ሁኔታ ብይን መስጠት አንችልም በሚል ውድቅ መደረጉንም ተናግረዋል።
‹ከታሰርኩ አራት ወር ሆኖኛል፤ የእስከዛሬው የፍርድ ቤት ሂደት የሚያሳየው ዐቃቤ ሕግ ዋና ዓላማው እኔን በወንጀል ከሶ የማስቀጣት ሳይሆን በተራዘመ የፍርድ ሂደት እኔን ማሰቃየት ነው› ልደቱ ቅሬታቸውን መግለጻቸውንም አዳነ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
የጤንነታቸው ሁኔታ ከአዲስ ማለዳ ለቀረበላቸው ጥያቄም አሁን ጤንነታቸው እንደተሻሻለ እና በጥሩ ጤንነት ላይ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
ችሎቱም የተሻሻለውን ክስ ለመስማት ለኅዳር 24 ከቀኑ 8 ሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here