ከመስከረም ስድስት ጀምሮ አዲሱን የብር ኖት መለወጥ እንደተጀመረ ይታወቃል በዚህም ብር ኖት የመለወጡ ሂደት በ ሦስት ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መወሰኑ ይታወቃል።
እስካሁን ያለው የብር ኖት መቀየር ሂደት በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል አሮጌውን ብር በአዲሱ የብር ኖት የመቀየር ሂደት የሚያበቃው ታህሳስ ስድስት 2013 ነው።
አዲሱን ብር መቀየር ከተጀመረ ኹለት ወር እንደሞላው ይታወቃል አሮጌውን የብር ኖት በባንክ ለመቀየር 24 ቀናት ይቀሩታል ያለው ባንኩ አሮጌው የብር ኖት ከህዳር 22 ቀን 2013 ጀምሮ ግን ማንኛውም ሰው በአሮጌው ብር ግብይት መፈፀም እንደማይችል ማዕከላዊ ባንኩ ተናግሯል።
ብሔራዊ ባንክ በአሮጌ ብሩ ለመገበያየት የቀረው ቀንም 10 ቀን ብቻ እንደሆነ ተናግሯል።በቀሪዎቹ ቀናትም ኅብረተሰቡ አሮጌዎቹን የብር ኖቶች ወደ ባንክ አምጥቶ መለወጥ እንዳለበት ማዕከላዊ ባንኩ አሳስቧል።
ታህሳስ 6ቀን 2013 የመጨረሻ ብር መቀየሪያ ቀን መሆኑ ታውቆ ኅብረተሰቡ በእጁ ያለውን አሮጌ ብር እንዲቀይር በድጋሜ አሳስቧል።
የፌደራል የክልል የከተማ አስተዳደር እና የፀጥታ አካላት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት የበኩላቸውን ድርሻ እንድትጫወቱ ብለዋል።
ቅጽ 2 ቁጥር 107 ኅዳር 12 2013



