የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች ላይ የጣለውን ዕግድ አነሳ

0
767

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች ላይ የጣለውን ዕግድ ከሰኞ ኅዳር 11/2013 ጀምሮ መነሳቱ ታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመሬት ልማት እና ማኔጅመንት በሥሩ ላሉ ተቋማት እንዲሁም ለአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ነሐሴ 20/2012 በጻፈው ደብዳቤ ከመሬት ጋር የተያያዙ አገልግሎቶች እንዳይሰጡ ማገዱ የሚታወስ ነበር።
የከንቲባ ፅሕፈት ቤት እና ካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ግዛው ዕግዱን አስመልክተው ለተቋማቱ በጻፋት ደብዳቤ የትኛውም የመሬት ተቋም ከነሐሴ 21/2012 ጀምሮ ስም ዝውውር፣ የካርታ ወይም የይዞታ ማረጋገጫ ሰነዶች ፣ የሕንጻና የቤት ሽያጭ እንዲሁም ተዛማጅ ተግባራት እና አገልግሎቶችን መስጠት ለጊዜው መታገዱን አመልክተው ነበር።
የመሬት አገልግሎቶች እንዲታገዱ የተደረገው ከመሬት እና መሬት ነክ አገልግሎቶች ጋር የተያየዙ አገልግሎቶች አተገባበር በጥሞና ለማጥናትና ይበልጥ ግልፅና ተገማች ለማድረግ አቅጣጫዎችን ለመተለም ብሎም ማስተካከያዋችን ለማድረግ እንደነበር በወቅቱ ተገልጿል።

ቅጽ 2 ቁጥር 108 ኅዳር 19 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here