የተጠቃለለ የአካል ጉዳተኞች ሕግ እየተዘጋጀ ነው

0
1043

የአካል ጉዳተኞችን መብት ጥሰት ለመከላከል፣ የእኩልነት እድገት፣ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያግዝ ‹‹የተጠቃለለ የአካል ጉዳተኞች ሕግ›› በመዘጋጀት ላይ መሆኑን የሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አስታወቁ።

የሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማሕበራት ፌደሬሽን ጋር በመተባበር የአካል ጉዳተኞች ቀን አከባበርን በሚመለከት ዛሬ ኅዳር 24/2013 በካፒታል ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

ሚኒስቴሩ የአካል ጉዳተኛ ዜጎች መብቶች እና ጥቅሞች እንዲከበሩ ጥረቶችን እያደረገ መሆኑን የጠቆሙት ሲሆን ብሔራዊ የማሕበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ፣ የአካል ጉዳተኞች የሥራ ሰምሪት መብትና ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮንቬንሽን አዋጅ፣ ብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች የድርጊት መርሃ ግብርና የአካላዊ ተሐድሶ ስትራቴጂ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪ የማስገባት መመሪያ መውጣቱንም ገልፀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here