በአዲስ አበባ በ200 ሚሊዮን ብር ወጪ ከተማ የማስዋብ ሥራ ሊከናወን ነው

0
564

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ200 ሚሊዮን ብር ወጪ የመንገድ ዳር አካፋዮችንና ፓርኮችን የማስዋብ ስራ ሊከናወን መሆኑን አስተዳደሩ አስታወቀ።
በዚህ ስራ ውስጥ 28 ሺሕ 162 ወጣቶች የስራ ዕድል እንደሚፈጠርላቸው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ገልጸዋል።
ከተማዋን የማስዋብ ተግባሩ ከጥር 1 ቀን 2013 ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ስራውን የሚያከናውኑ ወጣቶች ልየታ መካሄዱን አመልክተዋል።
ወጣቶቹ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ስልጠና አግኝተው ወደ ስራ የሚሰማሩ መሆኑንም ገልጸዋል።
ከስራ ዕድሉ ተጠቃሚ ወጣቶች መካከል 50 በመቶ የሚሆኑት ወጣቶች ሴቶች እንደሆኑ ጠቅሰዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ በዚህ በጀት ዓመት ለ280 ሺሕ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር የታቀደ ሲሆን እስካሁን 148 ሺሕ ለሚሆኑት የስራ ዕድል እንደተፈጠረ ተጠቁሟል።

ቅጽ 2 ቁጥር 111 ታህሳስ 10 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here