በስድስት ወራት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ 1.2 ቢሊዮን ብር ተሰበሰበ

0
658

ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ብቻ ተሰብስቧል የተባለው ይህ ገንዘብ ከመላው የሀገሪቱ ህዝቦችና ከዲያስፖራው በስጦታ፣ በቦንድ ግዢ እንዲሁም በ8100 A አጭር የጽሁፍ መልዕክት አማካኝነት መሰብሰቡ የተነገረ ሲሆን ይህም ባለፈው ዓመት ከተገኘው አጠቃላይ ገቢ ጋር ሲነጻጸር ከኹለት እጥፍ በላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የህዳሴው ግድብ ግንባታ ላለፉት አስር ዓመታት ከህብረተሰቡ በቦንድና ግዢና በስጦታ በሚገኝ ገቢ እንደቀጠለ የገለጸው የማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ ባሳለፍነው ዓመት መገባደጃ ላይ የመጀመሪያው የውሃ ሙሌት መጠናቀቁና በተፋሰስ አገራቱ መካከል የሚታዩ ኢፍትሃዊ አካሄዶች በማህበረሰቡ ላይ ቁጭትንና መነሳሳትን በመፍጠራቸው ለግድቡ የሚደረገውን ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረው ተነግሯል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 117 ጥር 22 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here