አንድ ሰው በመራጭነት ለመመዝገብ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡
- ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆን ይገባዋል፡፡
- ዕድሜው 18 እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡
- በምርጫ ክልሉ ቢያንስ ስድስት ወር የኖረ መሆን ይገባዋል፡፡
- ቢሆንም የአእምሮ ሕመም ያለባቸው ሰዎች እንዲሁም የመምረጥ መብታቸው በሕግ የታገደባቸው ሰዎች ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ቢያሟሉም እንኳን በመራጭነት መመዝገብ አይችሉም፡፡
- አንድ መራጭ በአንድ ምርጫ ጣብያ ከአንድ ጊዜ በላይ ወይም በሌላ ምርጫ ጣብያ በድጋሚ መመዝገብ አይችልም፡፡
- የመራጮች ምዝገባ እንደተጠናቀቀም የመራጮች መዝገብ በምርጫ ጣብያው ቅጥር ግቢ ውስጥ ለ10 ቀናት ይፋ ወጥቶ ሕዝብ በግልፅ እንዲያየው መደረግ አለበት፡፡ምንጭ፡- የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ሕግ
ቅጽ 2 ቁጥር 122 የካቲት 27 2013



