መራጮች በመራጭነት ለመመዝገብ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

0
900

አንድ ሰው በመራጭነት ለመመዝገብ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡

  1. ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆን ይገባዋል፡፡
  2. ዕድሜው 18 እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡
  3. በምርጫ ክልሉ ቢያንስ ስድስት ወር የኖረ መሆን ይገባዋል፡፡
  4. ቢሆንም የአእምሮ ሕመም ያለባቸው ሰዎች እንዲሁም የመምረጥ መብታቸው በሕግ የታገደባቸው ሰዎች ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ቢያሟሉም እንኳን በመራጭነት መመዝገብ አይችሉም፡፡
  5. አንድ መራጭ በአንድ ምርጫ ጣብያ ከአንድ ጊዜ በላይ ወይም በሌላ ምርጫ ጣብያ በድጋሚ መመዝገብ አይችልም፡፡
  6. የመራጮች ምዝገባ እንደተጠናቀቀም የመራጮች መዝገብ በምርጫ ጣብያው ቅጥር ግቢ ውስጥ ለ10 ቀናት ይፋ ወጥቶ ሕዝብ በግልፅ እንዲያየው መደረግ አለበት፡፡ምንጭ፡- የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ሕግ

ቅጽ 2 ቁጥር 122 የካቲት 27 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here