የአምራች ዘርፉን ለማበረታት የታሰበ ነው
የኢፌዲሪ ገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ የቀረጥ አዋጅ ማዘጋጀቱን ገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ገለጹ።
አዋጁ በቀረጥ አሰራር የሚታዩ ክፍተቶችን ሙሉ በሙሉ የሚፈታ አንደሆነ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል። አዋጁ የመጀመሪያ ውይይት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል። አክለውም የሚቀጥለው ሳምንት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ይደረግበታል ብለዋል።
በቀረጥ አሰራር ላይ የሚታዩ ችግሮችን ከሥር ከመሰረቱ አንደሚፈታ እና ሥር ነቀል ለውጥ እንደሚመጣ በሚኒስትር ዴኤታው የተነገረለት፣ ይህ አዋጅ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ይጠበቃል ተብሏል። አዋጁ የአምራች ዘርፉን የሚያበረታታ እና መዋቅራዊ ሽግግር የሚያመጣ እንደሆነም ተመላክቷል።
በተለይ የአምራች ዘርፉን ከማበረታት አንፃር አዲሱ የቀረጥ አዋጅ ትልቅ እድል የሚከፍት መሆኑን የጠቆሙት እየብ፣ በአዋጁ ላይ ለየትኛው ዘርፍ ምን ያክል ከቀረጥ ነፃ ማበረታቻ ያስፈልገዋል የሚለውን ጥያቄ በውል የሚመልስ ነው ብለዋል። የቀረጥ አዋጅ ትልቅ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ነው ያሉት እዮብ፣ “ጉዳዩ የሾለ፣ የተሳለ ብለዋ እንደማለት ነው” በመሆኑም በአግባቡ ሥራ ላይ ማዋል ያፈልጋል ብለዋል። አክለውም ግምሩክ አካባቢ የሚታዩ ችግሮችን የሚፈታ አዋጅ ነው ብለዋል።
አዲስ የተዘጋጀው የቀረጥ አዋጅ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን የሚፈታ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል። አዲስ ማለዳ ለሚንስትር ዴኤታው ኢትዮጵያ በ2013 በተያዘው በኹለተኛው ግማሽ ዓመት ተገቢ ባልሆነ ከቀረጥ ነፃ 12 ቢሊዮን ብር የገቢ ጉድለት ሊጋጥም እንደሚችል ግምሩክ ኮሚሽን መግለጹን በማስታወስ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር የሚፈቅደውን ተገቢ ልያሆ ከቀረ ነፃ እንደት ሊቀርፈው አስቧል በሚል ላቀረበችላቸው ጥያቄ አዋጁ ይህን ችግር ከሥር ከመሰረቱ ይቀርፈዋል ብለዋል። አንዱ አዋጁን ማዘጋጀት ያስፈለገበት ምክንያትም ከቀረጥ ነፃ የሚስፈልጋቸውን ዘርፎች ዝርዝርና የሚስፈልጋቸውን ምጣኔ ለመለየት ነው ብለዋል።
“አጠቃላይ የኢትዮጵያ የቀረጥና ግበር እፎይታ አሰራር ችግር ነበረው።” ያሉት ሚነስትር ዴኤታው ከውጭ በሚገቡ እቃዎች ላይ የሚሰጠው ከቀረጽ ነፃ ተገቢ ባለመሆኑ ከቀረጥ ነፃ የሚታጣውን ገቢ ያስቀርዋል ብለዋል። ከቀረጥ ነፃ ፍቃድ የሚሰጠው የኢትዮጵያ ንግድ ሚኒስቴር መሆኑን የጠቆሙት እዮብ፣ ይህ የሆነበት ምክንያት አድሎአዊ አሰራር እንዳይፈጠር መሆኑን አስታውሰዋል።
ከቀረጥ ነፃ አሰራር በእጅጉ ትኩረት የሚሻ በመሆኑ ከቀረጥ ነፃ ፍቃድ የመስጠት መብት ያለው ገንዘብ ሚንስቴር መሆኑን የጠቆሙት እዮብ ከኢንቨስትመንት ጋር ግንኙነት የላቸው ዘርፎች ላይ የኢትዮጵያ ማዕድን ሚኒስቴር እና የኢንቨስትንት ኮሚሽን ከቀረጥ ነፃ ፍቃድ እንደሚሰጡ ጠቁመዋል። ነግር ግን የፖሊሲ ክፍተት እንዳይኖር ከማድረግ አንፃር እና አሰራሩን ማዕከላዊ ከማድረግ አንፃር አዲሱ የቀረጥ አዋጅ የተሻለ አሰራር ይዞ እንደሚመጣ ተመላክቷል።
ኢትዮጵያ በ2013 በኹለተኛው በጀት ዓመት ተገቢ ባልሆነ ከቀረጥ ነፃ ተጠቃሚነት ምክንያት 12 ቢሊዮን ብር የገቢ ጉድለት ሊጋጥማት አንደሚችል የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ የሚታወስ ነው።
ኮሚሽኑ ለአዲስ ማለዳ አንዳስታወቀው በሚቀጥሉት ቀሪ የ2013 በጀት ዓመት ወራት ብቻ 12 ቢሊዮን ብር በቀረጥ ነፃ አማካኝነት የሚታጣውን ገቢ ከዚህ በፊት በተፈጸሙ ክዋኔዎች ላይ የተመሰረተ ጥናት በማድረግ የተሰላ መሆኑን ተጠቁሟል። ኮሚሽኑ ተጠባጭ መረጃዎችን በማሰባሰብ በሰነድ መረጃ በማስደገፍ ያገኘው መረጃ መንግሥት ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ መብት የሚሰጣቸው እቃዎች ላይ ገደብ ያስፈልጋል ሲል ጠቁሟል።
ቅጽ 2 ቁጥር 122 የካቲት 27 2013



