በተለያዩ ኤጀንሲዎች ውስጥ ተቀጥረው ከሚሰሩት የኤጀንሲ ሰራተኞች የፋይን ጄነራል ሰርቪስ የኤጀንሲው ሰራተኞች ማህበር የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ 11 56 /11 ላይ ያለው የ20 /80 እንዲሁም የሰራተኞች የስራ ላይ ደህንነት አዋጅ አለመተግበሩን እና አሁንም ይተገበራል ቢባልማ ትግበራው ላይ አመኔታ እንደሌላቸው ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ።
አዋጁ ከወጣ አንድ አመት ከሦስት ወር እንደሞላው የተናገሩት የሰራተኛ ማህበሩ ሰብሳቢ እና ሊቀመንበር ዮሀንስ አካሉ ሰራተኛው ተሰብስቦ ሰላማዊ ሰልፍ ሊወጣ አስቦ እንደነበር አስታውቀዋል።
ታህሳስ 2012 ላይ የወጣው ይህ አዋጅ ሳይተገበር በመቆየቱ እንዲሁም ሰራተኛው መናገር መጀመሩን ተከትሎ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ውይይት እያደረጉ እንደሆነ መረጃ ሲደርሳቸው ጥሪ ባይደረግላቸውም የማህበሩ ፀሀፊ የሆኑትን ስንታየሁ ደስታን በቦታው ልከው እንደነበር ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
በዚህም በውይይት መድረኩም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ሕገ ወጥ ሥራ እየተሰራ አንደሆነ በአንድ አገር ውስጥ መንግሥት የሌለ እስኪመስል ድረስ መመሪያ ወጥቶ አለመተግበሩ ተገቢ እንዳልሆነ ከተወያዮቹ መካከል ተነስቶ እንደነበር ተናግረዋል።
በዚህም የሰራተኛና ማህበራዊ ሚኒስቴሯ በተገኙበት ውይይት ከተደረገ በኋላ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለመገናኛ ብዙኃን ተገልፆ የወጣው አዋጅ ተግባራዊ እንደሚሆንና ሰራተኛውም የላቡን እንደሚያገኝ ቃል መገባቱን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
ከመጀመሪያ መመሪያውን ተግብሩ መመሪያ ወጥቷል ብለን የጠየቅነውም ክስም የመሰረተንነው አሰሪ ተቋማችንን ነው፤ነገር ግን የተያያዘ ነው ያሉት ሊቀመንበሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኛና ማህበራዊ ጎዳይ ውስጥ ያለ ሰው በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ስር የሰራተኞችን ጉዳይ የሚያይ ቦርድ ላይ ዳኛ ሲሆን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ውስጥ ደግሞ የስራ አስፈፃሚ ነው ብለዋል።
ስለዚህም ሰራተኛና ማህበራዊ በኩል ጥያቄያችንን ስናቀርብ ተገቢ የሆነውን ሕግ የሰጠውን መብት ተጠቅሞ ህጉ እንዲተገበር ህግ ፊት የጠሰጠውን ስልጣን ተገን እድርጎ በተዋረድ ያሉ የሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች የሰሩት ሥራ የለም ብለዋል።
የላባችነንን ነው የጠየቅነው መንግስት ባለበት አገር የወጣ አዋጅን ሊያውም ደሀው የሰራበትን የጉልበቱን አለመክፈል አግባብነት የለውም ሕግ ከወጣ በኋላ ተግባራዊ መሆን ነው ያለበት ይህም አለማቀፋዊ መመሪያ ነው መንግስት ይህንን አለማድረጉም እምነት እንድናጣበት አድረጎና ሲሉ ያላቸውን ቅሬታ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።
አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የኤጀንሲ ሰራተኞች ማህበሩ ፀሀፊ ስንታየሁ ደስታ እንተናገሩት ጥያቄውን በተደጋጋሚ እንዳነሱ እና እስካሁንም ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል።
እንደ ስንታየሁ ገለፃ በውይይቱ ላይ ሊከፈለን እንደሚገባ ቢወሰንም አሁን ድረስ ተፈፃሚነቱ ላይ እርግጠኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል፤ በኤጀንሲ የሚንገኝ ሰራተኞች የሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እና መብታችንን ለመጠየቅ አስበን ነበር ብለዋል።
አሁንም ቢሆን የሰራተኛውን ድምፅ ሰምተው ሳይሆን ምርጫው ስለተቃረበ አፋችንን ለማዘጋት በሚል ሀሳብ ይመስላል ውይይት እያደረጉ ያሉት ሲሉ ያላቸውን ስጋት ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
ያለብንን ችግር ተረድተው መፍትሄ ሊሰጡን ይገባል። በዋናነት የማስፈፀም ችግር በከፍተኛ መልኩ አለ ብለዋል።
አዋጁ የማይተገበር ከሆነ መውጣት አልነበረበትም ብለዋል። የስራ ቦታ ዋስትና የስራ ቦታ ደህንነት ለሰራተኛው የሚያስፈልገው እረፍት በአጠቃላይ የሰራተኛው መብት በኤጀንሲዎች ተግባራዊ እየተደረገ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
አዋጁ ላይ ያሉት መመሪያዎች ሊተገበሩ ይገባል አንድ አገር መንግስት እያለው ህግ የበላይ ሆኖ ሳለ የማይተገበርበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው ብለዋል።መንግስት ይህንን አዋጅ ሊያስተገብር ይገባል ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ግን መንግስት እንዴት ምረጡኝ ብሎ ሊጠይቅ ይችላል ብለዋል።
አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ላይ ያነጋገረቻቸው የሰራተኛና ማህበራዊ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት የሆኑት ደረጄ እንደተናገሩት በጉዳዩ ላይ ውይይት እያደረጉ እንደሆነና ውይይቱ ሳይጠናቀቅ መረጃ መስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል።ውይይቱ ሲጠናቀቅ እና ውሳኔ ሲወሰን ለሚዲያዎች እንደሚያስታውቁም አክለው ተግረዋል።
ቅጽ 2 ቁጥር 122 የካቲት 27 2013


