መገናኛ ብዙኀንና በ2013 የፓርቲዎች ምርጫ ዘመቻ በይፋ መጀመሩን ተከትሎ በእለቱ የሰሩት ዘገባ መልካም ቢሆንም ከዚያ ወዲህ ያለው የዘገባ ሽፋን ግን ወገንተኝነት የተሰተዋለበት በመሆኑ መጪው አገራዊ ምርጫ ላይ አሉታ ተጽእኖ እንዳይኖረው ስጋት አለኝ ብሏል፡፡
ይህንን የፓርቲዎቹን የምርጫ ዘመቻ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ሚዲያዎች ለገዥው ፓርቲም ይሁን ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የዘገባ ሽፋን ሲሰጡ ተስተውሏል። የግልም ይሁን የ “ መንግስት “ ብዙኃን መገናኛዎቹ የመጀመሪያው ሰሞን የፓርቲዎችን የምርጫ ዘመቻ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቶች ሽፋን መስጠታቸው መልካም ጅምር ሆኖ አልፏል።
ይሁንና የዘገባ ሽፋናቸው ምጣኔ በግርድፉ ሲታይ ውግንና የተስተዋለበት ነበር ማለት ይቻላል። በተለምዶ የ “መንግስት “ የሚባሉትና ለገዥው ፓርቲ ቅርበት ያላቸው ብዙኃን መገናኛዎች ለገዥው ፓርቲ ሰፋ ያለ ሽፋን ሲሰጡ በተመሳሳይ በተለምዶ የግል የሚባሉት ደግሞ ለ “ ተፎካካሪዎች” ሰፋ ያለ ሽፋን ሰጥተዋል። ይህ በሁሉም ዘርፎች ማለትም በ መደበኛ ብዙኃን መገናኛዎች “ Mainstream Media “ እና በ አዲሱ ትውልድ ብዙኃን መገናኛዎች “ Social/New Media “ የተስተዋለ ነው። ይህ በብዙኃን መገናኛዎቹ የተስተዋለው የ “ ፓርቲ ውግንና ዝንባሌ “ በሚቀጥሉት ጊዜያት በሚኖረው ነፃና ፍትሃዊ የምርጫ አዘጋገብና የምርጫ መረጃ ተደራሽነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳይኖረው ስጋት አለን። በመሆኑም የብዙኃን መገናኛዎች መማክርት /Media Council/ ፣ የጋዜጠኞች ማህበራት፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣንና ሌሎች ባለድርሻዎች በምርጫ ዘገባና ሽፋን ዙሪያ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል። አሳታፊ በሆነ መልኩ ጊዜያዊ ኮሚቴ ቢቋቋም መልካም እንደሆነ በመግለጫቸው አስታቀዋል።
ቅጽ 2 ቁጥር 123 መጋቢት 3 2013


