የየካቲት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 20.6 ሆኖ ተመዘገበ

0
1214

የጥር ወር አጠቃላይ ግሽበት 19.2 ነበረ ፤ በየካቲት ወር የ4 በመቶ ጭማሪ አሳይቶ 20.6 በመቶ መድረሱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ገልጿል።
የየካቲት ወር ምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ22.8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።
በእህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በያዝነው ወርም የቀጠለ ሲሆን ለምግብ ዋጋ ግሽበት መጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ኤጀንሲው ገልጿል።
በተጨማሪም አትክልትና ጥራጥሬ ዓይነቶች የዋጋ ጭማሪ አስመዝግበዋል ብሏል። በሌላ በኩል ስኳር፣ የምግብ ዘይት፣ ቅመማ ቅመም በርበሬ፣ ድንች እና ቡና የዋጋ ጭማሪ በዚህም ወር በመቀጠላቸው ለዋጋ ግሽበት ምጣኔ መጨመር አስተዋጽኦ አድርገዋል ተብሏል።
በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት የየካቲት ወር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ18.0 በመቶ ጭማሪ በማሳየት ፈጣን ዕድገት አሳይቷል ተብሏል።
ከምግብ ነክ ያልሆኑ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋና ምክንያቶች ውስጥ በተለይም በአልኮልና ትምባሆ ትምባሆ ፣ ልብስና ጫማ፣ አነቃቂዎች (ጫት)፣ የቤት እንክብካቤ እና ኢነርጅ (ማገዶና ከሰል) ፣ የቤት መስሪያ እቃዎች ፣ ህክምና ፣ ትራንስፖርት (ነዳጅ) እና ጌጣጌጥ (ወርቅ) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ነው ተብሏል።


ቅጽ 2 ቁጥር 123 መጋቢት 3 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here