ፔፕሲኮ በኮረና ቫይረስ ለተጎዱ ዜጎች የመቶ ቀናት የምገባ መርሃ ግብር አስጀመረ

0
1132

ፔፕሲኮ ከመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ለተጎዱ እና ጫና ለደረሰባቸው አካላት ከ8.3 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመቶ ቀናት የምገባ መርሃ ግብር ማስጀመሩን አስታወቀ፡፡
በፔፕሲኮ የበጎ አድራጎት ፋውንዴሽኑ አማካኝነት የሚመራው ይህ የድጋፍ መርሐ ግብር ከ8ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምግብ ድጋፍ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ባስከተለው ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ጫና በስፋት ተጋላጭ ለሆኑ የማኅበረሰብ አካላት ተደራሽ እንደሚያደርግ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል፡፡
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሥጋት እና የንግድ እንቅስቃሴ ገደብ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የምግብ ዋስትና አደጋ ላይ ጥሎታል፡፡ ለዚህ ዓለም አቀፋዊ የማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠትም ፔፕሲኮ ከታወቁ ግብረሰናይ ተቋማት ጋር በመጣመር በይበልጥ ጫናው ክንዱን ላሳረፈባቸው አካላት ለመድረስ እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት እያደረገሚገኝም ድርጅቱ አስታውል፡፡ የምግብ ይለግሱ ተስፋን ይቀጥሉ ፕሮግራም አቅመ ደካሞችን፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን በመደገፍ ከሚታወቀው ሀገራዊ የበጎ አድራጎት ድርጅት መቄዶንያ ጋር በጥምረት የሚከናወን ነው ተብሏል፡፡
ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የፔፕሲኮ መጠጦች ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ሰርጂኦ ፓያ “ምግብ ይለግሱ – ተስፋን ይቀጥሉ የተሰኘውን ፕሮግራም የቀረጽነው በወረርሽኙ ሳብያ ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን የማኅበረሰብ አካላት በአስፈላጊ ድጋፎች ለመድረስ ነው፡፡” ብለዋል፡፡
የመቄዶንያ ግብረ ሰናይ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ብንያም በለጠም በበኩላቸው በዚህ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ፕሮግራም ላይ ከፔፕሲኮ ጋር በጥምረት መሥራት በመቻላችን ለእኛ ትልቅ እድል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በዚህ ድጋፍ አማካኝነትም ከ100 በላይ ለሆኑ ተከታታይ ቀናት ለ2000 ሰዎች የምግብ ድጋፍ ለማድረግ እንደሚቻል ቢኒያም ገልጸዋል፡፡


ቅጽ 2 ቁጥር 124 መጋቢት 11 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here