በምእራብ ኦሮሚያ በግድያና ዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ 48 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

0
631

በምእራብ ኦሮሚያ ዞኖችና የተለያዩ አካባቢዎች በግድያና ዘረፋ ወንጀል ላይ ተሰማርተው የነበሩ 48 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል ክትትል ዘርፍ አዛዥ ግርማ ገላን ግንቦት27/2012 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “አባ ቶርቤ” በሚል ስም ተደራጅተው የሰዎችን ህይወት ሲያጠፉ የነበሩ ግለሰቦብ በተደረገው ፍተሻና ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።
በቄለም ወለጋ ዞን፣ በነቀምቴ እና በቡራዩ ከተሞች ሲፈፀሙ የነበሩ ጥፋቶችን በተመለከተ በጉዳዩ ላይ ትእዛዝ ሲሰጡ የነበሩ ሀይሎችን እና ጥፋቱን ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ አስታውቅዋል።
ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘም መንግስት ሙሉ ማስረጃ እንዳለውም ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን ተናግረዋል።
እነዚህ የጥፋት ሀይሎች 4 የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ወንጀሎችን ሲፈጽሙ እንደነበረም መግለፃቸውንም የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገልጿል።
ስልቶቹም በጫካ ውስጥ ታጥቆ መንቀሳቀስ፣ “አባ ቶርቤ” በሚል የተደራጀ ሀይል የመንግስት የስራ ሃላፊዎችንና ባለሀብቶችን ህይወት ማጥፋት፣ በአክቲቪስት ስም የተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ድረ ገፆችን በመጠቀም ህዝብ ውስጥ ውዥንብር መፍጠር እንዲሁም ምርጫ ላይ ሀይል ለመጠቀም አቅደው እንደነበረ ተደርሶበታል ብለዋል።
ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን አክለውም በኦነግ ሸኔ ስም በምእራብ ኦሮሚያ ቄለም ወለጋ ውስጥ 212 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን እና በሰዮ ከተማ ውስጥ ደግሞ 114 ሰዎች በዚሁ ሀይል ህይወታቸው ማለፉንም አስታውቀዋል።


ቅጽ 2 ቁጥር 124 መጋቢት 11 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here