ለሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች መተዳደሪያ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው
የፌደራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በየደረጃዉ የሚገኙ ተቋማትን የሚከታተሉ 538 የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎችን አደራጅቶ ወደ ሥራ ማስገባቱን ለአዲስ መለዳ አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቀው በፌደራል ደረጃ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድና በድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳር ሥር በሚገኙ ተቋማት ሥር የተማትን ብልሹ አሰራር እንዲከላከሉና እንድቆጣጠሩኝ ነው ያቋቋምኳቸው ብሏል። ከዚህ በፊት በፈደራል፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና በድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር ሥር የነበሩት የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች 170 ብቻ መሆናቸውን የፌደራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሙስና መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አክሊሉ ሙሉጌታ ለአዲስ ማለዳ አስታውሰዋል።
ቀደም ብሊ በውስን ተቋማት የነበሩ የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ተግባራቸው በተገቢው መንገድ እንዳልተወጡ ኮሚሽኑ ጠቁሟል። በዚሁ መሰረት ኮሚሽኑ በ2013 በሰራው የተጠናከረ ሥራ በሙሉ አቅማቸው የሚሰሩ 538 የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎችን መደራጀቱን አስታውቋል። ኮሚሽኑ ይህን ያደረገው በየተቋማት የሚፈጸሙ ሙስናዎችን በቅርበት የሚከታተልለት ትንንሽ ኮሚሽኖችን በየደረጃው ማስቀመጥ በማስፈለጉ ነው ተብሏል። እንዲሁም ከዚህ በፊት ተደራጅተው ሥራቸውን በተገቢው መንገድ ያልሰሩትን ኃላፊነታቸውነ በሚገባ እንደወጡና የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍል ያልነበራቸውን ተቋማት በየደረጃው በማደራጀት የሕዝብን ሀብት ከብክነት ለመከላከል እድል ይፈጥራል ተብሎለታል።
በተቋማት ሥር የሚገኙ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች “የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1236/2013” ተግባራዊ እስከሆነብት የካቲት 2/2013 ድረስ ተጠሪነታቸው ለተቋሙ የበላይ ኃላፊ እንደበር የኮሚሽኑ የሕግ ምክር፣ ትግበራና ልምድ ቅመራ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ገዛኸኝ ጋሻው ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። ነገረ ግን “የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1236/2013” አንቀጽ20 ንዑስ አንቀጽ ሦስት “የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ተጠሪነታቸው ለፌደራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ይሆናል” ይላሉ።
በመሆኑም አዋጅ ቁጥር1236/2013 ተግባራዊ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደርና በፌደራል ተቋማት ሥር የሚገኙ የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ተጠሪነታቸው ለኮሚሽኑ ሆኗል።
በዚሁ መሰረት ኮሚሽኑ የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎችን በየደረጃው እስከወረዳ ድረስ በማደራጀት የተቋማትን አሰራር እንድከታተሉለት እያደረገ ነው። ይሁን እንጅ ኮሚሽኑ እንዚህን በቅርቡ በሥሩ የሚስተዳድራቸውን የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች የሚመራበት ወጥ መመሪያ ስለሌለው መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑን ገዝሀን ለአዲስ ማለዳ ጠቁመዋል።
ኮሚሽኑ ባሳለፍነው መጋቢት 03/2013 የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎችን አሰራርና አደረጃጀት ለመወሰን የሚረዳ መመሪያ ለማዘጋጀት ከባለ ድርሻ አካላት የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት አድርጓል።
የግብዓት ማሰባሰቢያው የተካሄደው በቅርቡ በተሻሻለው የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1236/2013 መሰረት በማድረግ ነው። የኮሚሽኑ የሕግ ምክር፣ ትግበራና ልምድ ቅመራ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ገዛኸኝ እንደገለጹት የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች አሰራርና አደረጃጀት ኮሚሽኑ በሚያዘጋጀው መመሪያ መሰረት እንደሚወሰን በተሻሻለው የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀፅ 20 ንዑስ አንቀፅ 6 እና 7 ተደንግጓል ብለዋል።
በኮሚሽኑ የሥነምግባር መከታተያና ሙስና መከላከል ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አክሊሉ ሙሉጌታ በበኩላቸው የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ማቋቋም በሁሉም ተቋመት እስከ ወረዳ ድረስ ትንንሽ ፀረ ሙስና ኮሚሽኖችን ማቋቋም ማለት ነው ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ጠቁመዋል።
ቅጽ 2 ቁጥር 124 መጋቢት 11 2013



