የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝበ ውሳኔ የሚደራጅ ቢሮ ተቋቋመ

0
814

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔውን የሚያደራጅ በቦርዱ ስር የፕሮጀክት ቢሮ አቋቁሞ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡ ይህ የፕሮጀክት ቢሮ ዋናው የአገር አቅፍ ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት ባሉ የኦፕሬሽናል ስራዎች እንዳይዋጥ የሚያስችል ነው።
እስከሁን በፕሮጀክት ቢሮው የህዝበ ውሳኔ በጀት ተዘጋጅቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተልኳል እንዲሁም የህዝበ ውሳኔው አክሽን ፕላን (እቅድ) ተዘጋጅቷል ተብሏል። ቦርዱ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ያዘጋጀው በጀት ስምንት ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ነው። ገንዘቡ ከሌሎች የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ሲሆን ሪፈረንደሙ ከአገር አቀፍ ምርጫው ጋር በአንድ ቀንና በአንድ አይነት ዝግጅት የሚካሄድ በመሆን የወጪ ብክነት አስቀርቷል ተብሏል።


ቅጽ 3 ቁጥር 125 መጋቢት 18 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here