ምርጫ ቦርድ ሊከፈቱ የነበሩትን 30 የምርጫ ጣቢያዎች እንዳይቋቋሙ ወሰነ

0
897

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምርጫ ጣቢያዎች ያለአግባብ በሶማሌ ብሔራዊ ክልል መንግስት ሥር በሚገኙ ቀበሌዎች ስም ይፋ ተደርገዋል የሚል አቤቱታ ለቦርዱ ባቀረበው መሰረት በ8 ቀበሌዎች ሊከፈቱ የነበሩትን 30 የምርጫ ጣቢያዎች በአካባቢው እንዳይቋቋሙ ወስኗል።
የምርጫ ጣቢያዎች የአስተዳደር ወሰኖችን የሚወስኑ መገለጫዎች ባይሆኑም ምርጫ በምንም መልኩ የሰላም መደፍረስ ምክንያት እንዳይሆን በማሰብ በነበሩበት እንዲቀጥሉ መወሰኑን ገልጿል።


ቅጽ 3 ቁጥር 125 መጋቢት 18 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here