በስድስተኛው አገራዊ ምርጫን ለመታዘብ 155 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተመዝግበው 36 ድርጅቶች በ1ኛ ዙር ፍቃድ ማግኘታቸው ተከትሎ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በዘርፉ በሚሰማሩበት ወቅት በዓላማቸው መሰረት መንቀሳቀስ ይገባቸዋል ተብሏል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በምርጫው የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማግባባት፣ የመራጮች ትምህርት እና ምርጫ መታዘብ ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል።
የውጭ ድርጅቶች በምርጫ መታዘብም ሆነ ማስተማር በልዩ ሁኔታ በምርጫ ቦርድ ካልተጋበዙ በቀር ምንም ሚና አይኖራቸውም ሲሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ተናግረዋል።
ድርጅቶቹ ከምርጫ በፊት የመራጮች ትምህርት፣ የምርጫ ጊዜ ምርጫን መታዘብና ከምርጫ በኋላ ግጭት እንዳይከሰት ህዝቦችን የማረጋጋት እና አለመግባባቶች ቢኖሩ እንኳን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ የማድረግ ሚና እንዳላቸው ተነግሯል።
ቅጽ 3 ቁጥር 125 መጋቢት 18 2013



