የአውሮፓ ሕብረት ቀጣዩን ስድስተኛ አገራዊ ምርጫ እንዲታዘቡ ባለሙያዎቹን እንደሚልክ ኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሳለፍነው ማክሰኞ ግንቦት 3/2013 በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ከአውሮፓ ሕብረት በተጨማሪ ከአሜሪካ እና ሩሲያ የተውጣጡ ባለሙያዎች ምርጫውን ለመታዘብ እንደሚመጡ የውጪ ጉዳይ ቃል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከስምምነት መድረስ ባለመቻሉ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ አስቦ የነበረውን የምርጫ ታዛቢ እንዲቀር መወሰኑን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
የአውሮፓ ሕብረት የቀደመ ውሳኔውን ሰርዞ ምርጫውን ለመታዘብ ስለመወሰኑ እስካሁን ያለው ነገር የለም።
ሕብረቱ የሚልካቸው የምርጫ ታዛቢ ቡድን የሚሰማራበት ቁልፍ መለኪያዎች /ፓራሜትርስ/ ላይ ከመንግሥት ጋር ከስምምነት መድረስ አልተቻለም ብሎ ነበር።
ቅጽ 3 ቁጥር 132 ግንቦት 7 2013



