የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የምርጫ ጣቢያዎች መቃጠላቸውን ገለጸ

0
1136

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ(ኢሰመጉ) ግንቦት 5/2013 ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ደዋጨፋ ጃራ ልዩ የምርጫ
ጣቢያ፣ እንዲሁም በምዕራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ አባሮ ምርጫ ጣቢያ መቃጠላቸውን መረጃ እንደደረሰው ገልጿል፡፡
ኢትዮጰያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ ጊዜን ያራዘመ ቢሆንም፣ መራጮች የምርጫ ካርድ ለመውሰድ ሲሄዱ ካርድ አልቋል እየተባሉ እንደሚመለሱ ኢሰመጉ ገልጿል፡፡ ከመተከል ተፈናቅለው በቻግኒ ከተማ ራንች እና በጓንጓ ወረዳ በጊዜያዊ የመጠለያ
ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ቁጥራቸው 55 ሺሕ የሚሆኑ ተፈናቃዮች የመምረጥ መብታቸውን አስመልክተው ጥያቄ ቢያቀርቡም ተገቢውን ምላሽ አለማግኘታቸው በመግለጫው ተገልጿል፡፡
በዚህም ተፈፅመዋል ስለተባሉት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ኢሰመጉ በቀጣይ ምርመራ የሚያካሂድ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በአገራዊ፣ በአህጉራዊ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ላይ እውቅና ያገኙ የሰብአዊ መብቶች አደጋ ላይ መሆናቸውን ኢሰመጉ ገልጿል፡፡
የኢሰመጉ ምርመራ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መንግስት እነዚህን ጉዳዮች በማጣራት አስፈላጊውን አስቸኳይ እርምጃ ወስዶ፣ ጥሰቶቹን መግታት ካልቻለ የሰብአዊ መብቶች ቀጣይ እጣፋንታ ኢሰመጉን በእጅጉ እንደሚያሳስበው ጠቁሟል፡፡


ቅጽ 3 ቁጥር 132 ግንቦት 7 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here