የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባን እስከ ግንቦት 17 ቀን 2013 ድረስ ማራዘሙን አስታውቋል።
በየምርጫ ጣቢያዎቹ የሚደረገው የመራጮች ምዝገባ ቢጠናቀቅም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ መሰጠት እንዳለበት ቦርዱ መወሰኑን ገልጿል።
በኢንተርኔት የሚከናወነው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ምዝገባ በhttps://www.ovrs.gov.et በሚገኘው የመመዝገቢያ ማስፈንጠሪያ(ሊንክ) በመጠቀም እስከ ግንቦት 17/2013 ድረስ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምዝገባ ማስፈንጠሪያ በድረ-ገጽ www.nebe.org.et ላይም እንደሚገኝ ተጠቁሟል። የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች እንዲሁም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ይህንን የኦንላይን ምዝገባ በማስታወስ ምዝገባቸውን እንዲያከናውኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠይቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኢንተርኔት እንደሚከናወን ማሳወቁን ተከትሎ ምዝገባ ሲከናወን እንደነበር አስታውሷል።
ቅጽ 3 ቁጥር 133 ግንቦት 14 2013



