የወላይታ ሶዶ የኒቨርሲቲ ካውንስል አባላት በምርጫ ወቅት የመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎችን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ታከለ ታደሰ(ፕ/ር) በምርጫ ወቅት የሚፈጸሙ ጉዳዮች ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ ተግባራቸውን እንዲቀጥሉ የማድረግና ያለማድረግ ሚና ሊኖራቸው ስለሚችል መምህራን ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ወቅትና ከምርጫ በኋላ በመማር ማስተማርና በማህበረሰብ አገልግሎት ሥራ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ተማሪዎቹ በምርጫ ወቅት ወደ ቤተሰባቸው ሲሄዱ የመማሪያ ዶክመንቶችን (Teaching documents) በበቂ ሁኔታ በተለያዩ ዘዴዎች ተባዝተው ለተማሪዎች ሊሠጡ እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዪች ምክትል ፕሬዝዳንት ሙላቱ ዴአ(ዶ/ር) በበኩላቸው ሁሉም መምህራን በምርጫ ወቅት ተማሪዎች ወደ ቤተሰበቻው ሲሄዱ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ሥራ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ተማሪዎቹ ወደየቤተሰቦቻቸው ከመሄዳቸው በፊት አሁን እየተሰጡ ያሉ ትምህርቶችን በተቻለ መጠን በፍጥነት መጨረስ እንዳለበቸው አስቀምጠው፣ ትምህርቱ ተማሪዎቹ ወደ ቤተሰብ ጋር እስኪሄዱ የማያልቅ ከሆነ በሀርድና ሶፍት ኮፒ እንዲደርሳቸው መደረግ እንዳለበት ጠቁመዋል።
ቅጽ 3 ቁጥር 133 ግንቦት 14 2013



