በጉራፈርዳ ታጣቂዎች ጥቃት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በጠቅላላው180 ያህል ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል

0
864

በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የአካባቢው እና የፌድራል የጸጥታ አባላትን ጨምሮ 180 ያህል ዜጎች ህይወታቸው አጥተዋል ተባለ፡፡ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ፍቅሬ አማን ከንጹሀን ዜጎች በተጨማሪም 28 የጸጥታ አካላት የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ ሲሆን፣ ከ29 በላይ ደግሞ ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ተዳርገዋል ማለታቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡
21 ሺሕ 938 የአካባቢው ነዋሪዎች ጥቃት ሊሰነዘርብን ይችላል በማለት ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሰደዳቸው፣ እንዲሁም በጉራፈርዳ እና በደቡብ ቤንች ወረዳዎች ከ732 በላይ የቆርቆሮና የሳር ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተነግሯል፡፡
በአካባቢው የንግድ ፣የእርሻና ሌሎችም ማኀበራዊ እንቅስቃሴዎች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸው እንዲሁም የሕብረተሰቡ ማኀበራዊ መስተጋብርም ችግር ውስጥ መውደቁ ተገልጿል፡፡
ለሕብረተሰቡ ስጋት የሆኑት ታጣቂዎች በየጫካውና በሕብረተሰቡ መካከል ሆነው የተለያዩ ስልቶችን በመቀያየር እየተጠቀሙ አሁንም በጸጥታ ኃይሉና በንጹሀን ዜጎች ላይ አሰቃቂ ግድያና ዘረፋ እየፈጸሙ መሆኑ ተመላክቷል፡፡


ቅጽ 3 ቁጥር 134 ግንቦት 21 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here